Sunday 15 February 2015

የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ እና የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ !


ፌብርዋሪ 14, 2015 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎና በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የድርጅቱ አባላቶች የተገኙ ሲሆን የአባላት ስብሰባው አስቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በኖርዌጂያን የሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 13፡30 ተጀምሮዋል።

ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ በ 24 ዓመት የወያኔ አረመኒያዊ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉት እና በየእስር ቤቱ በግፍ ለሚስቃዮ ንጹሀን ዜጐች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጹሎት በማድረግ ስብሰባውን ያስጀመሩት ሲሆን በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመበር አቶ ዮሐንስ አለሙ አባላቱን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግር አቅርበው የዛሬው የአባላት ስብሰባ ከሌሎቹ ጊዜያት በሁለት ምክንያቶች የተለየ መሆኑን ለተሰብሳቢው ገልፀዋል ይሄውም፦
1 የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60 ኛ ዓመት የልደት በአል የሚከበርበት ቀን በመሆኑና





2 የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዩጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የተመሰረተበትን 10ኛ አመቱ ላይ መገኘቱ እንደሆነ በማስረዳት ድርጅቱ በእነኚህ አስር ዓመታት ውስጥ ብዙ አመርቂ ስራዎችን እንደሰራና ቅንጅት ይዞለት የተነሳው አላማ እስከ አሁን ድረስ ይዞ በመጓዝ ላይ ያለ ድርጅት በመሆኑ ስለዚህም በድርጅታቸው ኩራት የሚሰማቸው መሆኑን በመግለፅ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ወጣቶች እና ሴቶች እየሰሩ ያለውን ስራ አድንቀው ወጣቶች ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው በመሆኑ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ትግላቸውን አጠንክረው መቀጠል እንዳለባቸው በማሳሰብ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌንና በወያኔ መንግስት በግፍ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችን በትግላችን እናስፈታለን በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

በመቀጠልም የተለያዩ የስራ ክፍል ክንውን ረፖርት ለአባላቱ ያቀረቡ ሲሆን ከበርገን፣ ከስታቫንገር፣ እና ከትሮንዳይም የመጡየዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የስራ ኃላፊዎች በስድስት ወር ውስጥ ስለሰሩት ስራዎች እና ወደፊትም ሊሰሩ ያቀዱትን ስራዎች ለአባላቱ በዝርዝር አስረድተዋል።

በወቅቱ ከአባላቱ የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ለጥያቄዎቹም በድርጀቱ ሊቀንበር በአቶ ዮሀንስ አማካኝነት ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል:: በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሚረዳቸው ድርጅቶችን በማስመልከት በድርጅቱ በተወከሉት ሠዎች አማካኝነት ስለድርጅቶቹ አላማ እና ድርጅቶች እየሰሩ ስላሉት ስራዎች ሰፋ ያለ ግምገማ አቅርበዋል።

ከአባላት ስብሰባው በመቀጠልም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን 60ኛ አመት የልደት በአል አከባበር ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን ዝግጅቱንም በንግግር ያስጀመሩት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዮሀንስ አለሙ ሲሆኑ ስለ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አጭር ንግግር በማድረግ ነበር ፕሮግራሙን ያስጀመሩት ። በመቀጠልም የአንዳርጋቸውን ታሪክ የሚዳስስ አጭር ፊልም በወጣቶች ክፍል የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ማን ነው? በሚልህይወትታሪኩ ዙሪያ እና ለሀገሩ ያደረጋቸውን የትግል ተሞክሮዎች በቅርበት ከሚያውቋቸው ሰው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል። እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸውን የሚያወድሱና ስለጀግንነቱ የሚያወሩ የተለያዩ ግጥሞችም ቀርበዋል።



በመጨረሻም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ምስል የያዙ ኬኮች ከድርጅቱ ዋና ፅፈትቤት እና ትሮንድላንድ ቅርንጫፍ ፅፈትቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን በድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሁም በወጣቶችና ሴቶች ክፍል ተወካዮች የመልካም ልደት ኬኩ ተቆርሶ ስነስርአቱ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተደረሰው ላንቺ ነው ሀገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው በሚለው ዝማሬ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 22፡00 ተጠናቋል።


በመጨረሻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ወጣቶች ፕሮግራሙን በመዘጋጀትና
በመምራት ላደረጉት አስተዋጾ በድርጅቱ ና በስራ አስፈጻሚኮሚቴ ስም ምስጋና እናቀባለን!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ


No comments:

Post a Comment