Friday 27 February 2015

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ

ኢሳት 

ወኪላችን እንደዘገበው በሰቆጣ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ 
ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።

ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ 
አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ 
ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው።

ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።


No comments:

Post a Comment